እንኳን ደህና መጡ

ቤተሰቦችን ታሳቢ በማድረግ ወደተዘጋጀው ፒካቡ ፒክቸርስ ስቱዲዮ ውስጥ፣ የልጅዎን ምናብ ወደ ሕይወት ለማምጣት የሚያስችሉ እጅግ በጣም ብዙ ጭብጥ ያላቸው ሴታፖች (setups) እና የሚያምሩ አልባሳትን ያገኛሉ። ስቱዲዮአችን ሰፊ የመኪና ማቆሚያ፣ ለቤትና ውጪ ፎቶዎች የሚያገለግሉ ስፍራዎች እና መናፈሻ ቦታዎች እንዲሁም የመጠበቂያ ስፍራ፣ የውጪ መቀመጫ ስፍራ፣ ማጥቢያና መለወጫ ክፍሎች አሉት። የሆነ ነገር ለመያዝ ቢረሱም እንኳ ቆይታዎን የተሟላ ለማድረግ አስፈላጊና መሰራታዊ የሆኑ የሕፃናት ቁሳቁሶች ሁሉ ተዘጋጅተውልዎታል።

እንዲሁም ትውስታዎትን ዘላቂ ማስታወሻዎች ለማድረግ ሰፊ የህትመት ምርጫዎችን እናቀርባለን — ከእንጨት ፍሬሞች እና ከተነባበሩ አልበሞች ጀምሮ እስከ ኩባያዎች፣ ሳህኖች፣ ዲጂታል ማሳያዎች እና ሌሎችም ትዝታዎችን ለመፍጠርም ሆነ ለመጠበቅ የሚያስፈልግዎት ነገር ሁሉ እዚህ ይገኛል።

ፎቶዎች

ሙሉ በሙሉ በእርስዎ ፍላጎት እና ምርጫ የተዘጋጁ የፎቶ ስታይሎች በማስተካከል አዲስ ለተወለዱ ልጆች፣ ለልደቶች፣ ለበዓላት፣ ለቤተሰብ ፕሮግራሞች እንዲሁም ሌሎች የፎቶ ፍላጎቶችዎ የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጅተን እንጥብቅዎታለን።

የቤት ለቤት አገልግሎት

በቤትዎ መቆየት ይመርጣሉ?

የሚፈልጉትን የፎቶ ስታይሎች ያማከሉ እቃዎችን፣ አልባሳቶችን እና የፎቶ መሳርያዎቻችንን ይዘን በመምጣት እርስዎ መምጣት ሳይጠበቅብዎት በቤትዎ ምቾት እንዳሉ የልጆችዎንም ሆነ የቤተሰብ የፎቶ ፕሮግራሞችን እናዘጋጅልዎታለን

Address

Megenagna, near AMCE

Hours

Mon-Sun 9am-6pm